Labour Draft-1156-2019

in on March 8, 2021

Choose Your Desired Option(s)

ማውጫ

የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ

Content

Labour

ስለ አሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ የወጣ አዋጅ

አሠሪና ሠራተኛ የጋራ ራዕይ ኖሯቸው የሥራ ግንኙነቶቻቸውን መሠረታዊ በሆኑና በህግ በተደነገጉ መብቶችና ግዴታዎች ላይ በመመስረት አስተማማኝ የኢንዱስትሪ ሰላም፤ የዘላቂ ምርታማነት እና የገበያ ተወዳዳሪነት አቅም በመፍጠር ሀገራችን ለተያያዘችው ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት የማስመዝገብ ብሔራዊ ግብ በትብብርና በጋራ እንዲሰሩ ማድረግ ጠቃሚ በመሆኑ፤ ሠራተኞች እና አሠሪዎች የየራሳቸውን ማኅበራት በሙሉ ፈቃድና ነፃነት በማቋቋም በመረጧቸው ህጋዊ ወኪሎች አማካኝነት መብትና ጥቅማቸውን ለማስጠበቅና ግዴታዎቻቸውን በአግባቡ ለመወጣት የኅብረት ድርድር እንዲ ያደርጉ፤ በመካከላቸው የሚነሱ የሥራ ክርክሮችም የማኅበራዊ ምክክር ሥርዓትን ጨምሮ በሌሎች አማራጭ መድረኮች በተቀላጠፈ ሁኔታ መፍትሔ እንዲያገኙ የሚያስችል ሥርዓት መዘርጋት አስፈላጊ በመሆኑ፤ መሠረታዊ የሥራ ላይ መብቶችንና ግዴታዎችን ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ለኢንቨስትመንትና ሀገራዊ የኢኮኖሚ ዕድገት ግቦች መሳካት ምቹ ሁኔታን መፍጠር የሚያስችል የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አስተዳደር ሥርዓት መመስረት እንዲቻል፤ እንዲሁም የሥራ ሁኔታን፤ የሙያ ደህንነት፤ ጤንነትና የሥራ አካባቢ ጥበቃንና የሁለትዮሽ እና የሦስትዮሽ ማኅበራዊ ምክክር አሠራርን በማጠናከር በሕግ መሠረት የማማከርና የመቆጣጠር ተግባራትን እያመጣጠነ ሥራውን የሚያከናውን

LABOUR PROCLAMATION

WHERE AS, it is essential to ensure worker-employer relations are governed by basic principles of rights and obligations with a view to enabling workers and employers to secure durable industrial peace; sustainable productivity and competitiveness through cooperative engagement towards the all-round development of our country;
WHEREAS, it has been found necessary to lay down a working system that guarantees the rights of workers and employers to freely establish their respective associations and to engage, through their duly authorized representatives, in social dialogue and collective bargaining, as well as to draw up procedures for the expeditious settlement of labour disputes, which arise between them;
WHEREAS, there is a need to create favorable environment for investment and achievement of national economic goals without scarifying fundamental workplace rights by laying down well considered labour administration; and determine the duties and responsibilities of governmental organs entrusted with the power to monitor labour conditions; occupational health and safety; and environmental protection together with bilateral and tripartite social dialogue mechanisms;


ፌደራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ነሃሴ ፹፱ ቀን ፪ሺ፲፩ ገጽ ፲፩ሺ፮፻፺፪ Federal Negarit Gazette No. 89, 5th September 2019, Page# 11692
አካል ስልጣንና ተግባር መዘርዘርና መወሰን በማስፈለጉ፤

እነዚህን ከላይ የተመለከቱትን ዓላማዎች በትክክል መተግበር ይቻል ዘንድ የአሠሪና ሠራተኛ ግንኙነቶች የሚመሩባቸውን መሠረታዊ ሃሣቦች እና የሥራ ሁኔታዎችን የያዘ፤ ከመንግሥት አጠቃላይ የፖለቲካ የኢኮኖሚና ማኅበራዊ ፖሊሲ ጋር የተገናዘበ፤ ኢትዮጵያ ከፈረመቻቸው ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽኖችና ሌሎች ሕጋዊ ሠነዶች ጋር የተጣጣመ ሕግ ለማውጣት በሥራ ላይ ያለውን የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ በአዲስ መተካት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤ በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ ፶፭ (፩) እና (፫) መሠረት የሚከተለው ታውጇል:-

ክፍል አንድ

ጠቅላላ

፩. አጭር ርዕስ
ይህ አዋጅ “የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር ፩ሺ፩፻፶፮/፪ሺ፲፩” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡
፪. ትርጓሜ
በዚህ አዋጅ ውስጥ:-
፩/ “አሠሪ” ማለት አንድ ወይም ከአንድ በላይ የሆኑ ሰዎችን በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፬ በተመለከተው መሠረት ቀጥሮ የሚያሠራ ግለሰብ ወይም ድርጅት ነው፡፡
፪/ “ድርጅት” ማለት ለንግድ፣ ለኢንዱስትሪ፣ ለእርሻ፣ ለኮንስትራክሽን ወይም ለሌላ ሕጋዊ ዓላማ የተቋቋመ በአንድ አመራር የሚካሄድ ተቋም ነው፡፡
የድርጅቱን ተግባር ለማከናወን ከዋናው ድርጅት ተለይቶ የተሰየመ በአሠራሩ ወይም በአቋሙ ራሱን የቻለ ሥልጣን ያለው የድርጅት ቅርንጫፍ ራሱን የቻለ ድርጅት ሆኖ ይቆጠራል፡፡
፫/ “ሠራተኛ” ማለት በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፬ በተመለከተው መሠረት ከአሠሪ ጋር በቅጥር ላይ የተመሠረተ የሥራ ግንኙነት ያለው ግለሰብ ነው፡፡

political, economic and social policies of the Country;

WHEREAS, it has been found necessary to reformulate the existing labour law with a view to attaining the aforementioned objectives and in accordance with the and in conformity with the international conventions and other legal commitments to which Ethiopia is a party;

NOW,THEREFORE, in accordance with Article 55 (1) and (3) of the Constitution of the Federal Democratic Republic of Ethiopia, it is hereby proclaimed as follows:

PART ONE

GENERAL

1. Short Title
This Proclamation may be cited as the “Labour Proclamation No.1156/2019”.
2. Definitions
In this Proclamation unless the context provides otherwise:
1/ “Employer” means a person or an undertaking who employs one or more natural persons in accordance with Article 4 of this Proclamation.
2/ “Undertaking” means any entity established under a united management for the purpose of carrying on any commercial, industrial, agricultural, construction or any other lawful activity.
Any branch carrying on the activities of an undertaking which is designated separately and which enjoys operational or organizational autonomy shall be deemed to be a separate undertaking.
3/ “Worker” means a person who has an employment relationship with an employer in accordance with Article 4 this Proclamation.


ፌደራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ነሃሴ ፹፱ ቀን ፪ሺ፲፩ ገጽ ፲፩ሺ፮፻፺፫

Federal Negarit Gazette No. 89, 5th September 2019, Page# 11693
፬/ “ሚኒስቴር” ወይም “ሚኒስትር” ማለት እንደአግባቡ የሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ወይም ሚኒስትር ነው፡፡
፭/ “አግባብ ያለው ባለስልጣን ” ማለት በየክልሉ የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ ህጎችን የማስፈፀም ኃላፊነት የተሰጠው መንግስታዊ አካል ነው፡፡
፮/ “የሥራ ደንብ” ማለት በዚህ አዋጅና በሌሎች አግባብ ባላቸው ሕጎች የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ የሥራ ሰዓትን፣ የዕረፍት ጊዜን፣ የደመወዝ አከፋፈልና የሥራ አፈፃፀም ውጤት መለኪያ ዘዴን፣ የደኅንነት ጥበቃንና የአደጋ መከላከያን፣ የዲሲኘሊን ደንቦችንና አፈፃፀማቸውን እንዲሁም ስለሌሎች የሥራ ሁኔታዎች የሚደነግግ የውስጥ ደንብ ነው፡፡
፯/ “የሥራ ሁኔታ” ማለት በአሠሪና ሠራተኞች መካከል ያለ ጠቅላላ ግንኙነት ሲሆን ይህም የሥራ ሰዓትን፣ ደመወዝን፣ ፈቃዶችን፣ ሠራተኞች ከሥራ በሚሰናበቱበት ጊዜ የሚገባቸውን ክፍያዎች፣ ጤንነትና ደኅንነት፣ በሥራ ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው ሠራተኞች የሚከፈል ካሣ፣ ሠራተኞች ከሥራየሚቀነሱበትን ሁኔታ፣ የቅሬታ አቀራረብ ሥርዓቶችንና የመሳሰሉትን ያጠቃልላል፡፡
፰/ “ክልል”ማለት በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ ፵፯(፩) የተጠቀሰ ማንኛውም ክልል ሲሆን ለዚህ አዋጅ አፈፃፀም የአዲስ አበባና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደሮችን ይጨምራል፡፡
፱/ “ማኅበራዊ ምክክር” ማለት የአሠሪና ሠራተኛ ማኅበራት በሁለትዮሽ ወይም መንግሥትን ጨምሮ በሦስትዮሽ መድረክ ማኅበራዊ አገልግሎቶች ስለሚስፋፉበት፣ በአሠሪና ሠራተኛ መካከል ስላሉ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ጉዳዮች መረጃ በመለዋወጥና ምክክር ወይም ድርድር በማድረግ መግባባት ላይ የሚደርሱበት ሂደት ነው።
፲/ “የሥራ መሪ” ማለት በሕግ ወይም እንደድርጅቱ የሥራ ጠባይ በአሠሪው በተሰጠውየውክልና ሥልጣን መሠረት የሥራ አመራር ፖሊሲዎችን የማውጣትና የማስፈፀም ሥልጣን ያለው ወይም ሠራተኛን የመቅጠር፣ የማዘዋወር፣ የማገድ፣ የማሰናበት ወይም
4/ “Ministry” or “Minister” means the Ministry or Minister of Labour and Social Affairs respectively.
5/ “Appropriate authority” means, a Regional state organ vested with the power of implementing labour laws.
6/ “Work rules” means internal rules which govern, subject to the provisions of this Proclamation and other relevant laws, working hours, rest period, payment of wages and methods of measuring work done, maintenance of safety and prevention of accidents, disciplinary measures and their enforcement as well as other conditions of work.
7/ “Condition of work” means the entire field of labour relations between workers and employers including hours of work, wage, leave, payments due to dismissal, workers health and safety, compensation to victims of employment injury, dismissal because of redundancy, grievance procedure and any other similar matters.
8/ “Regional state” means any State referred to in Article 47(1) of the Constitution of Federal Democratic Republic of Ethiopia, and includes the Addis Ababa and Dire Dawa city administrations.
9/ “Social dialogue” means a process of information exchange, dialogue or negotiation of bilateral or tripartite nature between employer and employees or involving the Government on economic and social issues of mutual interests towards arriving at common understanding.
10/ “Managerial employee” means an employee who, by law or delegation of the employer, is vested with powers to lay down and execute management policies, and depending on the type of activities of the undertaking, with or without the aforementioned powers an employee who is vested with the power to

ፌደራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ነሃሴ ፹፱ ቀን ፪ሺ፲፩ ገጽ ፲፩ሺ፮፻፺፫ Federal Negarit Gazette No. 89, 5th September 2019, Page# 11694
የመመደብ ተግባሮችን የመወሰን ሥልጣን ያለው ግለሰብ ሲሆን፣ እነዚህን የሥራ አመራር ጉዳዮች አስመልክቶ የአሠሪውን ጥቅም ለመጠበቅ አሠሪው ሊወስደው ስለሚገባው እርምጃ በማንም ሳይመራ የራሱን የውሳኔ ሃሣብ የሚያቀርብ የሕግ አገልግሎት ኃላፊን ይጨምራል፡፡
፲፩) “ወሲባዊ ትንኮሳ” ማለት በንግግር፣ በምልክት ወይም በሌላ ማናቸውም አድራጎት አንዱ ሌላውን ከፈቃዱ ውጭ ለወሲባዊ ተግባር ፈቃደኛ እንዲሆን ማባበል፣ መገፋፋት፣ ተፅዕኖ ማሳደር ነው፡፡
፲፪/ “ወሲባዊ ጥቃት” ማለት ኃይል የተቀላቀለበት ወሲባዊ ትንኮሳ ወይም የዚሁ ድርጊት ሙከራ ነው፡፡
፲፫/ “የግል ሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲ” (ከዚህ በኋላ ኤጀንሲ እየተባለ የሚጠራ) ማለት በሀገር ውስጥ የሥራ ስምሪት አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ህጋዊ ፈቃድ ኖሮት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ከሠራተኛው ገንዘብ ሳይቀበል:-
ሀ) የሥራ ውል ተዋዋይ ወገን ባለመሆን በአገር ውስጥ ሥራና ሠራተኛን የማገናኘት፤ ወይም
ለ) ከሠራተኛው ጋር የሥራ ውል ስምምነት በማድረግ ሠራተኛውን ለአገር ውስጥ ሥራ ለአገልግሎት ተጠቃሚ ድርጅት የሚያቀርብና ሠራተኛውን የማስተዳደር ኃላፊነት ያለው ሰው ወይም ሁለቱን አገልግሎቶች አጣምሮ የሚሰጥ ሰው ነው፡፡
፲፬/ “ፈቃድ” ማለት በግል ሥራና ሠራተኛ አገናኝነት ሥራ ላይ ለመሰማራት የሚያስችል አግባብ ባለው ባለሥልጣን ለግል ሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲ የሚሰጥ የምስክር ወረቀት፡፡
፲፭/ “በሰራተኞች መካከል ልዩነት ማድረግ” ማለት ብሔርን፣ ዘርን፣ ቀለምን ፆታን፣ ሐይማኖትን፣ የፖለቲካ አመለካከትን፣ ኤች.አይ.ቪን/ ኤድስን፣የአካል ጉዳትን እና ሌላ ሁኔታን መሠረት በማድረግ የሠራተኛውን በእኩልነት የመስተናገድ ወይም እኩል እድል ሁኔታን የሚያስቀር ወይም የሚያጠብ ማለት ነው፡፡
hire, transfer, suspend, layoff, dismiss or assign employees, and includes a legal service head who recommend measures to be taken by the employer regarding such managerial issues, using his independent judgment, in the interest of the employer.
11/ “Sexual harassment” means to persuade or convince another through utterances, signs or any other manner, to submit for sexual favor without his/her consent.
12/ “Sexual violence” means sexual harassment accompanied by force or an attempt thereof.
13/ “private employment agency” (herein after “Agency “) means any legally licensed person, to provide one or two of the following local Employment services without charging directly or indirectly any fee from the worker:
a) Local employment exchange service without being a party to an employment relation; or
b) Deploying of employees under its authority to the service of a service user enterprise, by entering into contract of employments with such employees; or combines both services.
14/ “License” means a certificate to be issued by a competent organ certifying that the entity is qualified to engage in private employment exchange service.
15/ “Discrimination” any distinction, exclusion or preference made on the basis of nation, race, color, sex, religion, political opinion, national extraction, social origin, HIV/AIDS status, disablement and others which has the effect of nullifying or impairing equality of opportunity or treatment in employment or occupation.
Publish Year
Publish Number
Document No Draft-1156-2019
Page Range
Docket No
Document Category
Publication Date
Effective Date
File Type PDF
File Size 2.6M
Document Version 1.0
Document Tag

0 Downloads

Share Now!

Legislation Information

Labour Draft-1156-2019

 • Price
  :

  $0.00

 • Released
  :

  March 8, 2021

 • Last Updated
  :

  March 8, 2021

 • File Included
  :

  PDF

 • File Size
  :

  2.6M

Printed Version

Labour Draft-1156-2019

0 0 votes
Document Rating
Subscribe
Notify of
0 Comments
Inline Feedbacks
View all comments
0
Would love your thoughts, please comment.x
()
x